У нас вы можете посмотреть бесплатно Ethiopia-Eritrea Tension | Melketa | ምልከታ Episode 004 |ከጦርነት ወደ ሰላም፣ ከሰላም ወደ ጦርነት የኢትዮጵያ-ኤርትራ አዙሪት или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
ሰላም ወዳጆች እንደሚታወቀው የኢትዮጵያና ኤርትራ ግንኙነት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የጦርነት ውጥረት እየታየበት ነው። የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ በቅርቡ ኤርትራን በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ለማቀጣጠል እየሰራች እንደሆነ ከሰዋል። ሙላቱ ተሾመ በፅሁፋቸው የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የፕሪቶሪያ ሰላም ስምምነትን ለማፍረስ እየሰሩ ነው ብለዋል።ኤርትራ በበኩሏ ይህንን ክስ በጠንካራ ቃላት ውድቅ ያደረገች ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት የውስጥ ችግሮቹን ወደ ውጭ ለማስተላለፍ እየሞከረ ነው ብላለች። በሌላ በኩል፣ ኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባህር የሚወስድ መውጫ ለማግኘት እያደረገች ያለው ጥረት ውጥረቱን እያባባሰው ነው። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) የአሰብ ወደብን ብቻ ሳይሆን መላውን የኤርትራ ግዛትን የመጠቅለል ፍላጎት አላቸው የሚል ክስ ከወደ ኤርትራ ተደጋግሞ ይሰማል። በተጨማሪም፣ የኢትዮጵያ የጦር ኃይሎች ኤርትራን እንደ ጠላት አድርገው መፈረጃቸውን የሚያመለክት ዘገባ አለ። ይህ ሁኔታ ሁለቱን አገሮች ወደ ጦርነት ሊያመራ የሚችል አደገኛ ሁኔታ እንደፈጠረ ተንታኞች እየገለጹ ነው። ይህ ውጥረት በአካባቢው ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያሳድር እንደሚችልም ይታመናል፣ የአፍሪካ ህብረትና ዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ ሁኔታውን በጥንቃቄ መከታተል ከጀመሩም ውለው አድረዋል። በዛሬው ፕሮግራማችን በሁለቱ ሀገራት መካከል አልመገባባትን እያባባሱ ካሉ ጉዳዮች መካከል፡ የባህር በር ጉዳይ፦ ማለትም ኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባህር የሚያደርስ መውጫ ለማግኘት እያደረገች ያለው ጥረት በተለይም የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የአሳብ ወደብን ለማግኘት ያላቸው ፍላጎት። የፖለቲካ ልዩነቶች፡ ይህም ኢትዮጵያ ከትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር (ሕወሓት) ጋር የሰላም ስምምነት መፈረሟ ኤርትራን ማስቆጣቱ እንዲሁም ኤርትራ የፕሪቶሪያ ሰላም ስምምነትን ለማፍረስ እየሰራች እንደሆነ በኢትዮጵያ በኩል መነገሩ። ከዚህም ባሻገር በሁለቱ ሃገራት መሀከል አሁንም ያልተፈቱ የድንበር ጉዳዮች መኖራቸው። ቀጠናዊ ተፅዕኖ፡ በምስራቅ አፍሪካ ፖለቲካ ሁለቱ ሃገራት ከፍተኛ ሚና አላቸው። ኢትዮጵያ የኤርትራ መንግስት በተለያዩ ጉዳዮች ቀጠናዊ ፖለቲካውን በተመለከት ትከሳለች። ከነዚህም ውስጥ ኤርትራ ከግብጽና ሶማሊያ ጋር አጋርነት መፍጠሯ፣ ኢሳያስ በሰሜን ኢትዮጵያ በተለይም በአማራ ክልል ግጭትን ለማቀጣጠል መጣር እና ከሕወሓት አንጃ ጋር በማበር የፕሪቶሪያ ሰላም ስምምነትን የማፍረስ ጥረት እንዲሁም የአካባቢው አለመረጋጋት ማባባስ ይገኙበታል። የዛሬው ፕሮግራማችን እየተቆሰቆሰ ያለውን የኢትዮጵያ እና ኤርትራ የግጭት አዙሪት እንተነትናለን። የቀድሞው የኢትዮጵያ ሬድዮ ጋዜጠኛ ፋሲል ግርማ በትንታኔው አብሮን ይቆያል። በተጨማሪም በፕሮግራማችን በ2019 ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ በተፈጠርው የእሳት አደጋ ለአባት እና ልጅ ህይወት መቀጠፍ ምክንያት ከሆነው የቤት አከራይ ፍርደኛ ሀበሻ ቤት አከራዮች እና ተከራዮች ምን ይማራሉ? አዲሱ የአሜሪካ ቪዛ ማሳደስ ህግ ምን ይላል? ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ በፖሊስ በተተኮሰበት ጥይት ህይወቱን ያጣው ውጣት ጉዳይ የሚሉት ይዳሰሳሉ። ፕሮግራማችን ለብዙዎች እንዲደርስ share ያድርጉ።