У нас вы можете посмотреть бесплатно በእግዚአብሔር ቤት ለዘላለም እኖራለው ክፍል 8 или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
1.2 መስዋዕት 2. ሄኖክ ዘፍ 5:21-24 ፣ ዕብ 11:5-6 ፣ ሮሜ 12:1 📌 ሄኖክ ከ65 አመቱ በኋላ ለ300 አመታት አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር በማድረግ እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘ ሰው ነው። 📌 እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መስዋዕት በእምነት የሆነ መስዋዕት ነው። መታዘዝ የራሳችንን ፈቃድ መሰዋትን እና የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማስተናገድ ይጠይቃል። 📌 ለሄኖክ እግዚአብሔር ወደ እሱ አይደለም የመጣው ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ነው ወደ ህልውናው የወሰደው። 3. ኖህ 📌 ላሜህ ልጁን ኖህን በስሙ አማካኝነት ለእግዚአብሔር ሰጥቶት ነበር። 📌 ኖህ በእግዚአብሔር ፊት ሞገስን ያገኘው ፃድቅ ስለሆነ እና አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ስላደረገ ነው። 📌 ኖህ የጥፋት ውሃው አብቅቶ ከመርከብ እንደወጣ የመጀመሪያ የሰራው መሰዊያ ነበር። 📌 ኖህ ለእግዚአብሔር መስዋዕት ስለሰዋ እግዚአብሔር አዳም እና ሄዋንን ባርኳቸው የነበረውን በረከት ነው የባረከው። እግዚአብሔር ኖህን የባረከበት በረከት ሚስጥር መታዘዝ እና መስዋዕት ነው። 3. አብርሃም ፣ ይስሃቅ እና ያዕቆብ 📌 አብርሃም ከአባቱ ቤት ታዞ ወጥቶ ባረፈበት ቦታ የመጀመሪያ የሰራው መሰዊያ ነበር። 📌 አብርሃም ለእግዚአብሔር በአባቱ ቤት ሆኖ አይደለም መሰዊያን የሰራለት። ነገር ግን ታዞ ከወጣ በኋላ ባረፈበት ምድር ነው መሰዊያን የሰራው። ታዞ ወጥቶ በሄደበት ቦታ መሰዊያን ሲሰራ ግን እግዚአብሔር መኖሪያውን አደረገለት። ⁉️ ሰው ከፀደቀ በኋላ የበረከትን ህይወት ሳይለማመድ ሊኖር እንዴት ይችላል? ⁉️ ፃድቅስ መሆን በራሱ ለመባረክ በቂ አያደርግም? 📌 ሎጥ በኢየሱስ ሳይቀር የተመሰከረለት ፃድቅ ሰው ነበር። ነገር ግን ከአብርሃም ጋር ከተለያየ በኋላ ህይወቱ የበረከት አልነበረም። 📌 ሎጥ ተባርኮ የነበረው ከአብርሃም ጋር በመኖሩ ነበር። 📌 የህይወታችን ምንጭ ከመሰዊያችን እንጂ በአይን ሲታይ የእግዚአብሔር ገነት ከሚመስል ነገር አይደለም። 📌 ሎጥ ፃድቅ የነበረ ቢሆንም መስዋዕትን የሚሰዋ ሰው ግን አልነበረም። አብርሃም ደግሞ በደረሰበት ቦታ ሁሉ መሰዊያን ሰርቶ ለእግዚአብሔር የሚሰዋ ነበር። 📌 በዚህም ምክኒያት ሎጥ መጀመሪያም ተባርኮ የነበረው ፣ የተነጠቀው ሀብት የተመለሰለት ፣ በሰዶም እያለ እንዳይጠፋ የተረፈው በአብርሃም አማካኝነት ነበር። ፃድቃን ይድናሉ ፤ መስዋዕትን የሚሰዉ አምላኪዎች ግን ከመዳንም አልፈው ይባረካሉ።