• ClipSaver
  • dtub.ru
ClipSaver
Русские видео
  • Смешные видео
  • Приколы
  • Обзоры
  • Новости
  • Тесты
  • Спорт
  • Любовь
  • Музыка
  • Разное
Сейчас в тренде
  • Фейгин лайф
  • Три кота
  • Самвел адамян
  • А4 ютуб
  • скачать бит
  • гитара с нуля
Иностранные видео
  • Funny Babies
  • Funny Sports
  • Funny Animals
  • Funny Pranks
  • Funny Magic
  • Funny Vines
  • Funny Virals
  • Funny K-Pop

#ተአምር скачать в хорошем качестве

#ተአምር 12 дней назад

скачать видео

скачать mp3

скачать mp4

поделиться

телефон с камерой

телефон с видео

бесплатно

загрузить,

Не удается загрузить Youtube-плеер. Проверьте блокировку Youtube в вашей сети.
Повторяем попытку...
#ተአምር
  • Поделиться ВК
  • Поделиться в ОК
  •  
  •  


Скачать видео с ютуб по ссылке или смотреть без блокировок на сайте: #ተአምር в качестве 4k

У нас вы можете посмотреть бесплатно #ተአምር или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:

  • Информация по загрузке:

Скачать mp3 с ютуба отдельным файлом. Бесплатный рингтон #ተአምር в формате MP3:


Если кнопки скачивания не загрузились НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru



#ተአምር

ስንክሳር ዘወርኀ ታኅሣሥ 7 አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ታኅሣሥ ሰባት በዚች ቀን በአባ መቃርስ ገዳም በደብረ ሲሐት የሚኖር አባ ዳንኤል አረፈ ። ይህም አባ ዳንኤል ስሟን እንጣልዮስ አስኝያ የነበረች ንግሥት በጥሪቃን የገነዛት ነው እርሷም ከሞቷ በኋላ እንጂ ሴት እንደሆነች አልታወቀችም ነበር ። በአንዲት ቀንም ወደ እስክንድርያ አገር ከረድኡ ጋር ሲጓዝ ስሙ ምህርካ የሚባል እብድ አገኘ ብዙ እብዶችም ይከተሉታል ለአገርሰዎችም በእውነት ያበደ ይመስላቸው ነበር አባ ዳንኤልም እጁን ይዞ ወደ ሊቀ ጳጳሳቱ ወስዶ ትሩፋቱን ተጋድሎውን ነገረው እንዲነግራቸውም በአማሉት ጊዜ ከዝሙት ጦር በመሸሽ ራሱን እብድ እንዳስመሰለ ነገራቸው ሰምተውም እግዚአብሔርን አመሰገኑት ። በአንዲትም ዕለት ወደ አንዲት አገር ደረሰ በዚያም አውሎጊስ የሚባል ለድኆች የሚራራ እንግዳም የሚቀበል ደንጊያ በመውቀር የሚኖር ሰው አገኘ እርሱንም ተቀብሎ በደስታ አሳደረው መልካም ሥራውንም በአየ ጊዜ ድኆችን የሚረዳበት ገንዘብን ለአውሎጊስ ይሰጠው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ስለርሱ ለመነ ጌታችንም በሕፃን አምሳል ተገለጠለትና ገንዘብ ባገኘ ጊዜ ጠባዩን እንዳይለውጥ አንተ ትዋሰዋለህን አለው አባ ዳንኤልም አዎን እዋሰዋለሁ አለ ። ከዚህም በኋላ አውሎጊስ በድስት የመላ ወርቅን አግኝቶ ያንን ይዞ ወደ ንጉሥ ሒዶ የጭፍራ አለቃ ሆኖ ተሾመ ጠባዩንም ለወጠ ። ጠባዩንም እንደለወጠ አባ ዳንኤል ሰምቶ ሊመክረውና ሊገሥጸው ሔደ የአውሎጊስ ወታደሮችም ለመሞት እስኪደርስ ድረስ ደበደቡት በዚህም እያዘነ ሳለ ያ ሕፃን በሕልም ታየው አባ ዳንኤልንም ለምን በሌላ ሰው ነገር ገባህ ብሎ እንዲሰቅሉት አዘዘ ። ከዚህም በኋላ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም መጥታ ለሕፃኑ ሰገደች እግሮቹንም እየሳመች ስለ አባ ዳንኤል ለምና ከስቅለት አዳነችው ። ከዚህም በኋላ ሌላ ንጉሥ በነገሠ ጊዜ አውሎጊስን ሊገድለው ፈለገው ያን ጊዜ አውሎጊስ ሸሸ ወደ አገሩም ደርሶ ወደ ቀድሞ ሥራው ተመለሰ ። በአንዲት ቀንም በሌሊት በበረሀ ውስጥ በጨረቃ ብርሃን ሲጓዝ በተራራ ላይ ተቀምጣ ሴት አገኘ ጠጉሩዋም ሥጋዋን ሁሉ ሸፍኖአል እየተጋደለች ሠላሳ ስምንት ዓመት የኖረች ናት ምሥጢርዋንም ሁሉ ነግራው ከዚህ በኋላ አረፈች ። ከዚህም በኋላ በአንዲት ዕለት የልዮንን ደብዳቤ ሰዎች አምጥተው በሕዝብ ፊት አነበቧት አባ ዳንኤልም ዘሎ የልዮንን ደብዳቤ ነጥቆ ቀደዳትና የኬልቄዶን ሃይማኖት የተገወዘ ነው አለ ወታደሮችም አይተው ደበደቡት ከገዳሙም አሳደዱት ። በአንዲት ዕለትም አባ ዳንኤል ከደናግል ገዳም ደርሶ ደጁን አንኳኳ አባ ዳንኤልም እንደሆነ አውቀው ከፈቱለትና በደስታ ተቀበሉት ከእነርሱም አንዲቷ ራሷን እብድ አስመስላ በደጅ የምትተኛ አለች ስለርሷ እመ ምኔቷን ጠየቃት እርሷም እብድ ናት አለችው ። እርሱም መስተጋድልት ቅድስት ሴት እንጂ እብድ እንዳልሆነች ነገራት ። እብድ የተባለችውም በሌሊት ተነሥታ የከበራችሁ እኅቶቼ ስለ አሳዘንኳችሁ ይቅር በሉኝ ብላ ጽፋ ያንን ትታ ታጣች ደናግሉም እጅግ አዘኑ ተጸጸቱም ። በውስጡ ብዙ ደናግል የሚኖሩበት ገዳም ነበረ መዝጊያውም የጸና ነው ። ገንዘባቸውንም ይበረብሩአቸው ዘንድ ሰይጣን ወንበዴዎችን በላያቸው አስነሣ የወንበዴዎች አለቃም በመራቀቅ በራሱ ላይ ቆብ አድርጎ በአባ ዳንኤል አምሳያ ለብሶ ደጃፋቸውን ሒዶ በማንኳኳት አባ ዳንኤል ነኝ አለ አይተውም ከፈቱለት በደስታም ተቀብለው እግሩን አጠቡትና ስለ በረከት የእግሮቹን እጣቢ በየፊታቸው ረጩት ከውስጣቸው አንዲት ዕውር ነበረች ውኃው ሲነካት ዐያኖቿ በሩላት ደናግሉም አንተ አባ ዳንኤል ንዑድ ክቡር ነህ አሉት የሽፍቶቹም አለቃ አይቶ ደነገጠ ተጸጸተም ከአባ ዳንኤልም ዘንድ መንኲሶ የሚጋደል ሆነ ። ዕረፍቱም በቀረበ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ነገረው ጥቂት ጊዜም ታመመ ክብር ይግባውና ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጸለየና በሰላም አረፈ ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ጻድቅ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን ። በዚችም ቀን የብፅዕት ዲዮጥርስ መታሰቢያዋ ነው እግዚአብሔርም በጸሎቷ ይማረን ለዘላለሙ አሜን ። በዚችም ቀን ለታወቀች እስዋን ለተባለች ገዳም አበ ምኔት የሆነ የሚጋደል ቅዱስ አባት አባ ማቴዎስ አረፈ ። ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ ጀምሮ በፈሪሀ እግዚአብሔር ጸንቶ ያደገ ነው ከገዳማትም በአንዱ መንኲሶ በጾም በጸሎት ተወስኖ የሚጋደል ሆነ በገዳሙም ውስጥ ለራሱ መኖሪያ ሠራ ደቀ መዛሙርቱ አባ ሰራብዮንና አባ ኅድራ ሥራውን ተጋድሎውንና ተአምራቱን እንደተናገሩ መረብንም በመሥራት ሽያጩን ለድኆች ይመጸውታል ። እነርሱም እንዲህ ብለው ተናገሩ በአንዲት ዕለት ከማደሪያው በውጭተቀምጠን ሳለ በማደሪያው ውስጥ አንዱ ከሌላው ጋር እንደሚነጋገርሁኖ ቃልን ሰማን በገባንም ጊዜ ከእርሱ በቀር ያገኘነው የለም ። አባታችን ሆይ በውጭ ሳለን ከአንተ ጋር ሰው እንደሚነጋገር ድምፅ ሰምተን ነበር በገባን ጊዜ ከአንተ በቀር ያገኘነው የለም አልነው ። በብዙ ትሕትና እንዲህ አለን ልጆቼ ሆይ የምትጠብቀኝን የሞት ፃዕርና ሥቃዮችን ለነፍሴ በማሳሰብ የኃጢአቴን ብዛት አስቤ ከራሴ ጋርተነጋገርኩ ። ለድኃ ማቴዎስ ወዮለት ንጽሕናን ቅድስናን በለበሱ የመላእክት የጻድቃንና የሰማዕታት ጉባኤ አንድነት በአለበት በልዑል እግዚአብሔር መንበር ፊት ራቁቱን ያቆሙታልና እንዲህም አድርጎ የኃጥአንን ሥቃይ የጻድቃንን መልካም ዋጋ ለልጆቹ አስተማራቸው ። ቅዱስ ማቴዎስም በሠራት ገዳም ውስጥ ጸሎትን ተጋድሎን አገልግሎትን በማድረግ ጸንቶ ኖረ ገዳሙንም በአባ ጳኩሚስ ስም አከበረ እርሷም የታወቀች ሰሌን ያለባት ተራራ ናት ። ርኩሳን የሆኑ ረቂቃን ሰይጣናትም በቀንና በሌሊት የሚያስፈራሩት ሆኑ በየዓይነቱ በተለያየ መልክ ፊት ለፊት እያያቸው እነርሱ በፊቱ ይሮጣሉ በኋላውም ይከተሉታል እርሱ ግን አይፈራቸውም እጁንም ዘርግቶ በመስቀል ምልክት ሲአማትብ በዚያን ጊዜ በነፋስ ፊት እንዳለ ጢስ ይበተናሉ ። በአንዲትም ዕለት ጥቂት እንጀራና ውኃ በመንቀል ከገዳም ውስጥ ይዞ በበረሀ ውስጥ ወደአለች ዋሻው እንዲሔድና እርሱ በማግሥቱ እስቲመጣ በዚያ እንዲጠብቀው ረድኡን ሰራብዮንን አዘዘው ። ሰራብዮንም ወደ ዋሻው ሲደርስ ሁለት ታላላቅ አራዊት በውስጥ ተኝተው አገኘ ፈርቶ በሩን ዘግቶ ከዐለት ቋጥኝ ላይ ወጣ ። ከዚህም በኋላ አባ ማቴዎስ የዳዊትን መዝሙር እያነበበ መጣ ረድኡንም አይቶ ፈገግ ብሎ ሳቀ ሰራብዮን ሆይ እኔ ወዳንተ እስከምመጣ ወደ ዋሻው ውስጥ ለምን አልገባህም አለው ። እርሱም ረድኡ አባቴ ሆይሁለት ታላላቅ አውሬዎች ተኝተው ስለ አገኘሁ እነርሱን ፈርቼ አልገባሁም አለው ። ንጽሐ ነፍስ ያለው የዋህ የሆነ የተመሰገነ አረጋዊም ልጄ እመነኝ እኔ ከእነርሱ ጋር ስኖር ዐሥራ ሁለት ዓመት ሆነኝ ያሳደግኋቸውም እኔ ነኝ ይህንንም እንጀራና ውኃ እንድታመጣ ያዘዝኩህ ለእነርሱ ነው አለው ። ከዚህም በኋላ በሩን በከፈተ ጊዜ እነዚያ አውሬዎች ወደርሱ መጥተው ቅዱስ አባ ማቴዎስን እግሮቹን ላሱ ባልንጀሮችም ሁነውት በታላቅ መለማመጥ ተገዙለት ያንንም ውኃ ከገንዳ ላይ አፍስሶላቸው ጠጡ እንጀራውንም በሉ ከዚያም በኋላ ወደ ዱር ሔዱ ። ይህም አባ ማቴዎስ የዜናው መሰማት በቦታው ሁሉ እስከመላ ድረስ ተአምራትን እያደረገ ኖረ በየዓይነቱ በሆነ ደዌ የተያዙትን ያመጡለታል ። እርሱም በላዩ በአደረች በእግዚአብሔር ኃይል ይፈውሳቸዋል ።ከተአምራቶቹም አንዱ በአንዲት ቀን ጋኔን ያደረበት ዲዳ ሰውን ወደርሱ አመጡ ቅዱስ ማቴዎስንም በአየው ጊዜ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ሰውዬውን ከምድር ላይ ጣለው ቅዱሱም በዘይት ላይ ጸለየ በመስቀል ምልክትም አማትቦ ቀባው በዚያንም ጊዜ ድኖ አእምሮው ተመለሰ የሚሰማና የሚናገርም ሆነ ደስ ብሎትም ወደቤቱ ሔደ ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ጻድቅ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን ። በዚችም ዕለት ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ክብርይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ እንደሚወለድ በከበሩ ነቢያት አፍ ለመሰበኩ መታሰቢያ ሆነ ይቅርታውና ቸርነቱ ከእኛ ጋር ለዘላለሙ ይኑር አሜን ። ታኅሣሥ ፯ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ፩.ስብከተ ነቢያት ፪.አባ ዳንኤል ገዳማዊ ፫.አባ ማቴዎስ ገዳማዊ ፬.ብጽዕት ዲዮጥርስ ወርኀዊ በዓላት ፩.ሥሉስ ቅዱስ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፪.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ፫.አባ ሲኖዳ የባሕታውያን አለቃ ፬.አባ ባውላ ገዳማዊ ፭.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ፮.ቅዱስ አግናጥዮስ ለአንበሳ የተሰጠ ይህን በመጀመሪያ እወቁ ። በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም ። ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና ። ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ ። ፪ዼጥ. ፩፥፳

Comments
  • #የታሕሣሥ 8 ሥንክሳር #የአቡነ ኪሮስ አማላጅነት የደረሰለት 12 дней назад
    #የታሕሣሥ 8 ሥንክሳር #የአቡነ ኪሮስ አማላጅነት የደረሰለት
    Опубликовано: 12 дней назад
  • ዓመታዊ የታኅሣሥ ገብርኤል በዓል ሥርዓተ ቅዳሴ እና ትምህርተ ወንጌል እሑድ ታኅሣሥ ፲፱ ፳፻፲፰ ከደ/ኃ/ቅ/ገ/ እና  ቅ/ዮ/መ/የኢ/ ኦ/ተ/ ቤ/ክWash,DC
    ዓመታዊ የታኅሣሥ ገብርኤል በዓል ሥርዓተ ቅዳሴ እና ትምህርተ ወንጌል እሑድ ታኅሣሥ ፲፱ ፳፻፲፰ ከደ/ኃ/ቅ/ገ/ እና ቅ/ዮ/መ/የኢ/ ኦ/ተ/ ቤ/ክWash,DC
    Опубликовано:
  • ዋቻሞ IMCS ከሐዋሳ IMCS | የጥያቄ እና መልስ ውድድር | ምዕራፍ 8 - የደረጃ | በካቶሊክ የዩኒቨረስቲ ተማሪዎች መካከል | IMCS 23 часа назад
    ዋቻሞ IMCS ከሐዋሳ IMCS | የጥያቄ እና መልስ ውድድር | ምዕራፍ 8 - የደረጃ | በካቶሊክ የዩኒቨረስቲ ተማሪዎች መካከል | IMCS
    Опубликовано: 23 часа назад
  • ገድለ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ 12 дней назад
    ገድለ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ
    Опубликовано: 12 дней назад
  • 🌻🌻3ቱ ሞትን ያልቀመሱት ሰወች ታሪክ - የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ - 1 месяц назад
    🌻🌻3ቱ ሞትን ያልቀመሱት ሰወች ታሪክ - የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ -
    Опубликовано: 1 месяц назад
  • የታሕሣሥ 5 ሥንክሳር#ገብረ መንፈስ ቅዱስ #ጴጥሮስ እና ጳውሎስ#ፆታዋን የደበቀች ቅድስት #እግዚአብሔር  በቅዱሳኑ 2 недели назад
    የታሕሣሥ 5 ሥንክሳር#ገብረ መንፈስ ቅዱስ #ጴጥሮስ እና ጳውሎስ#ፆታዋን የደበቀች ቅድስት #እግዚአብሔር በቅዱሳኑ
    Опубликовано: 2 недели назад
  • 1 месяц назад
    "New Mezmur" 💒ሚካኤል ሐመልማለ ወርቅ💒(michael hamelmale work) ዘማሪ እዮብ መስፍን/ zemari eyob mesfin/
    Опубликовано: 1 месяц назад
  • የታሕሣሥ 9 ሥንክሳር#ያለደም መፍሰስ ሰማዕት የሆ አባ በአሚንን ያውቃሉ?#እስትንፋሰ ክርስቶስ #ፃድቃን 10 дней назад
    የታሕሣሥ 9 ሥንክሳር#ያለደም መፍሰስ ሰማዕት የሆ አባ በአሚንን ያውቃሉ?#እስትንፋሰ ክርስቶስ #ፃድቃን
    Опубликовано: 10 дней назад
  • Part 2 / 28 December 2025 2 часа назад
    Part 2 / 28 December 2025
    Опубликовано: 2 часа назад
  • የታኅሣሥ ገድለ ቅድስት አርሴማ 13 дней назад
    የታኅሣሥ ገድለ ቅድስት አርሴማ
    Опубликовано: 13 дней назад
  • የታሕሣሥ 14 ሥንክሳር#በአመት አንድ ጊዜ  የምታፈራው ዛፍ #ቅዱስ መርምህናም#ብርሃን 6 дней назад
    የታሕሣሥ 14 ሥንክሳር#በአመት አንድ ጊዜ የምታፈራው ዛፍ #ቅዱስ መርምህናም#ብርሃን
    Опубликовано: 6 дней назад
  • ቀጥታ ከዳግማዊ ኩልቢ #ቤተ ውዳሴ ቲዩብ#subescribe💗like💗shere Трансляция закончилась 8 часов назад
    ቀጥታ ከዳግማዊ ኩልቢ #ቤተ ውዳሴ ቲዩብ#subescribe💗like💗shere
    Опубликовано: Трансляция закончилась 8 часов назад
  • የልደት መዝሙር ፣ በኤፍራታ ምድር ፣ ሊቀ መዘምራን ይልማ ሐይሉ /lke Mezemran Ylma Hailu 3 недели назад
    የልደት መዝሙር ፣ በኤፍራታ ምድር ፣ ሊቀ መዘምራን ይልማ ሐይሉ /lke Mezemran Ylma Hailu
    Опубликовано: 3 недели назад
  • የታሕሣሥ 10 ሥንክሳር#ሰዎችን ከሐጢአት መውደቅ የሚጠብቅ አባት #አባ ኒቆላዎስ ዘሀገረ ሜራ#ይህንን ቀን ያውቃሉ? 10 дней назад
    የታሕሣሥ 10 ሥንክሳር#ሰዎችን ከሐጢአት መውደቅ የሚጠብቅ አባት #አባ ኒቆላዎስ ዘሀገረ ሜራ#ይህንን ቀን ያውቃሉ?
    Опубликовано: 10 дней назад
  • ⭕️የመላዕክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ⭕️በዴሴ ጢጣ ሚካኤል አስገራሚ የበዓል አከባበር .. 1 месяц назад
    ⭕️የመላዕክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ⭕️በዴሴ ጢጣ ሚካኤል አስገራሚ የበዓል አከባበር ..
    Опубликовано: 1 месяц назад
  • የታሕሣሥ 16 ሥንክሳር #እስራኤልን ለ40 አመት በሠላም ያስተዳደረ መስፍንና ነቢይ ያውቃሉ ?# 4 дня назад
    የታሕሣሥ 16 ሥንክሳር #እስራኤልን ለ40 አመት በሠላም ያስተዳደረ መስፍንና ነቢይ ያውቃሉ ?#
    Опубликовано: 4 дня назад
  • ኣገድስቲ 80 ቃላት ቋንቋ እንግሊሽ ንጀመርትን ማእኮሎትን 7 часов назад
    ኣገድስቲ 80 ቃላት ቋንቋ እንግሊሽ ንጀመርትን ማእኮሎትን
    Опубликовано: 7 часов назад
  • ታሪኻዊ ምብጻሕ ብጹዕ ወቅዱስ ቀዳማዊ ባስልዮስ 6ፓትርያርክ ኦ.ተ.ቤ.ኤርትራ ናብ ኖርወይ 2025 1 месяц назад
    ታሪኻዊ ምብጻሕ ብጹዕ ወቅዱስ ቀዳማዊ ባስልዮስ 6ፓትርያርክ ኦ.ተ.ቤ.ኤርትራ ናብ ኖርወይ 2025
    Опубликовано: 1 месяц назад
  • የሕዳር 13 ሥንክሳር#የብዙ ብዙ ቅዱሳን መላዕክት #13ቱ ግኁሣን አባቶች #የሽፍቶች እግር ታጥቦ ሽባውን ፈወሰ 1 месяц назад
    የሕዳር 13 ሥንክሳር#የብዙ ብዙ ቅዱሳን መላዕክት #13ቱ ግኁሣን አባቶች #የሽፍቶች እግር ታጥቦ ሽባውን ፈወሰ
    Опубликовано: 1 месяц назад
  • 🌻🌻ገድለ አዳም እና ሀዋን #ክፍል #5 1 месяц назад
    🌻🌻ገድለ አዳም እና ሀዋን #ክፍል #5
    Опубликовано: 1 месяц назад

Контактный email для правообладателей: [email protected] © 2017 - 2025

Отказ от ответственности - Disclaimer Правообладателям - DMCA Условия использования сайта - TOS



Карта сайта 1 Карта сайта 2 Карта сайта 3 Карта сайта 4 Карта сайта 5