У нас вы можете посмотреть бесплатно 001 ከሌሎች እግር ሥር ተንበርክከናል - Keleloch Eger Ser Tenberkekenal или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
“ከሌሎች እግር ሥር ተንበርክከናል” የሚል ርእስ የተሰጠው ይኽ ትምህርት የተቀረጸው ግንቦት 16 ቀን 1995 ዓ.ም. ሲሆን ቦታው በክቡር አባታችን አለቃ አያሌው ታምሩ መኖሪያ ቤት ውስጥ ነው፡፡ የትምህርቱ ዋነኛ ትኩረት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በግንቦት ወር ከሚዘከሩ መንፈሳውያን መታሰቢያዎች አንዱ በሆነው እና ሲኖዶስ በመባል በሚታወቀው የቤተ ክርስቲያን ልዩ ጉባዔ ላይ ነው፡፡ በ12ቱ ቅዱሳን ሐዋርያት የተመሠተው የቤተ ክርስቲያን ልዩ ጉባዔ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት የሚሠራ ስለመሆኑ፣ ከመጀመሪያዪቱ ቤተ ክርስቲያን ጀምሮ እስከ አሁኑ ዘመን ድረስ በነበረው ሂደት በሰላምም ሆነ በችግር ጊዜ ስለአደረገው አስተዋጽኦ ተገልጧል፡፡ የቀደመውን የሲኖዶስ አሠራር መሠረት በማድረግ የዘመናችንን ሲኖዶስ የሚገመግመው ይኽ ትምህርት የደረስንበትን የውድቀት ደረጃ በግልጽ እያሳየ ለመፍትሔው እንድንተጋ የቀሰቅሳል፡፡ ለመፍትሔው የማንተጋ ከሆነ ሊመጣብን ያለውን ጥፋትና መከራ ጠቁሟል፡፡ (ትምህርቱ የሰተጠው ከ17 ዓመታት በፊት መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ ክቡር አባታችን የሰጉበት ነገር ሁሉ በተጨባጭ እየተፈጸመ ካለበት ወቅት ላይ ደርሰን የዓይን ምሥክሮች ሆነናል፡፡)