У нас вы можете посмотреть бесплатно ልጅ ኢያሱ/Lij Iyasu የዳግማዊ አፄ ምኒልክ አልጋ ወራሽ или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
ልጅ ኢያሱ ጥር 28 ቀን 1887 ዓ.ም. በወሎ ክፍለ ሀገር በደሴ ከተማ ተወለደ። የኢያሱ አባት የወሎ ገዥ የነበሩት ንጉሥ ሚካኤል ሲሆኑ እናቱ ወይዘሮ ሸዋረጋ ደግሞ የዳግማዊ አፄ ምኒልክ ሴት ልጅ ነበሩ። የኢያሱ አባት ራስ ሚካኤል የወሎ ገዥና የምኒልክ የረጅም ጊዜ ወዳጅ ነበሩ። ንጉሥ ሚካኤል አስቀድሞ መሐመድ አሊ ተብለው ይጠሩ የነበረ ሲሆን ሥልጣናቸውን ለማስጠበቅ በቦሩ ሜዳ ጉባኤ በአፄ ዮሐንስ 4ኛ ትዕዛዝ ክርስትናን እስከሚቀበሉበት ጊዜ ድረስ ሙስሊም ነበሩ። በሕይወታቸው መጨረሻ አካባቢ አፄ ምኒልክ አልጋ ወራሽ ሳይሾሙ ቢሞቱ ያቋቋሟት መንግሥት በእርስ በርስ ጦርነት ተበታትና በአውሮፓ ቅኝ ገዥ ኃይሎች ልትበላ እንደምትችል በመገንዘብ የአልጋ ውርስ ጉዳይ አሳሳቢ ሆኖባቸው ነበር። አራት ሊሆኑ የሚችሉ ወራሾችም ነበሯቸው። በተለመደው የሰሎሞናዊ የውርስ ሥርዓት መሠረት ቀጣዩ ቀጥተኛ አባታዊ የዘር ሀረግ የነበራቸው የምኒልክ አጎት ልጅ የነበሩት ደጃዝማች ታዬ ጉልላት ነበሩ። ሌሎቹ ሦስቱ ወራሾች በሙሉ በእናታዊ የዘር ሐረግ በኩል የመጡ ነበሩ። ከእነዚህም መካከል የመጀመሪያው የልጅ ልጃቸውና ልጃቸው ወይዘሮ ሸዋረጋ ምኒልክ ከመጀመሪያ ባላቸው ከወዳጆ ጎበና የወለዱት ደጃዝማች ወሰን ሰገድ ነበር። ከሴት መስመር ሁለተኛው ወራሽ ታናሹ የልጅ ልጃቸው ልጅ ኢያሱ ነበር። በመጨረሻም ከሴት መስመር ሦስተኛዋ ወራሽ የምኒልክ ልጅ የነበሩት ልዕልት ዘውዲቱ ሲሆኑ የእቴጌ ጣይቱ የወንድም ልጅ ከሆኑት ራስ ጉግሳ ወሌ ጋር ትዳር መስርተው ነበር። በሕይወታቸው መጨረሻ አካባቢ አፄ ምኒልክ ታዬ ጉልላትን በአልጋ ወራሽነት ግምት ውስጥ ማስገባት አልፈለጉም። ወሰን ሰገድ ደግሞ ደካማ ጤንነት ላይ የነበረ ሲሆን በሳንባ ነቀርሳም ይታመም ነበር። መኳንንቱ ሴትን እንደ መሪያቸው እንደማይቀበሉ ግልጽ ስለነበር ዘውዲቱ በዚህ ጊዜ አልታሰበችም። ምኒልክም ወደ ደብረ ሊባኖስ መንፈሳዊ ጉዞ ባደረጉ ጊዜ በጸና በሽታ ታምመው ነበር። ከዚህም በኋላ ምኒልክ ለሹማምንቱ ኢያሱ አልጋ ወራሻቸው እንደሆነ አሳወቁ። ይሁን እንጂ ኢያሱ ገና ልጅ በመሆኑ ምኒልክ አልጋ ወራሹ ለአቅመ አዳም እስኪደርስ ድረስ ጊዜያዊ አስተዳዳሪ (እንደራሴ) እንዲሾሙ የቀረበውን ሐሳብ ተቀበሉ። ኢያሱ ለአቅመ አዳም እስኪደርስ ድረስም ቢትወደድ ተሰማ በሙሉ ሥልጣን ጊዜያዊ አስተዳዳሪ (ባለሙሉ እንደራሴ) ሆነው ይሾማሉ። በ1902ም ልጅ ኢያሱ የጎጃሙን የራስ ኃይሉን ሴት ልጅ ሰብለ ወንጌል ኃይሉን አገባ። አፄ ምኒልክ ልጅ ኢያሱን አልጋ ወራሽ እንዲሆን ከወሰኑ ብዙም ሳይቆይ በድጋሚ ታመሙ። በዚህም ጊዜ እቴጌ ጣይቱ የእንጀራ ልጃቸውን ልዕልት ዘውዲቱን እና የልጃቸውን ባል ራስ ጉግሳ ወሌን በኢያሱ ምትክ ለማድረግ ሞከሩ። በርካታ መኳንንትም የእቴጌ ጣይቱን ተግባር በመቃወም ተነሱ። ጥቅምት 18 ቀን 1902 ዓ.ም. አፄ ምኒልክ ከገጠማቸው ከከባድ በሽታ በኋላ ምኒልክ ልጅ ኢያሱን አልጋ ወራሽ አድርገው መርጠው ራስ ቢትወደድ ተሰማ ናደው ደግሞ ጊዜያዊ አስተዳዳሪ ሆኑ። አዲሱ ጊዜያዊ አስተዳዳሪ ሥልጣናቸው በሕይወት ባሉት ነገር ግን በህመማቸው ምክንያት መንቀሳቀስ ባልቻሉት አፄ ምኒልክ ብቻ ሳይሆን በእቴጌይቱም ጭምር ሲዳከም ተመለከቱ። ለምሳሌ፦ በአዲስ አበባ ከሚገኙ የውጭ አገራት ቆንስላ ጽሕፈት ቤቶች የሚቀርቡ ጥያቄዎች ለራስ ተሰማ ሳይሆን ለራሳቸው እቴጌይቱ እንዲቀርቡ እቴጌይቱ አጥብቀው ይከራከሩ ነበር። ከዚህም በላይ ራስ ተሰማ ራሳቸው ይታመሙ ስለነበር አቅማቸው እንደደከመና ነገሮችን በቶሎ ማከናወን እንደማይችሉ ይታሰብ ነበር። የእቴጌይቱን ተጽዕኖ በቆራጥነት ለመገደብ የቻሉት የመኳንንት ቡድንና የንጉሠ ነገሥቱ የጥበቃ ኃላፊ በጋራ ያቀነባበሩት መፈንቅለ መንግሥት የተሳካላቸው ራስ ተሰማንና ሀብተ ጊዮርጊስን በማሳመን ነበር። እነዚህ ክስተቶችም የንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት እንዲዳከም አደረጉ፤ በዚህም ወቅት የውጭ ጉዳይ በተመሳሳይ ሁኔታ ተጎድቷል። ይህ ቢሆንም ሃሮልድ ማርከስ የራስ ተሰማ መኖር "የሚኒስትሮችን አለመግባባትና ሴራ የገታና የማዕከላዊ ሥልጣን መኖሩን ማስታወሻ ነበር" ብሎ አስረድተዋል። ራስ ተሰማ በነበሩበት ጊዜ ልጅ ኢያሱ በአዲስ አበባ የመጀመሪያውን የፖሊስ ኃይልን ጨምሮ የምኒልክን የዘመናዊነት መርሃ ግብር ቀጠለ። በሚያዚያ 3 ቀን 1903 ዓ.ም. ራስ ተሰማ ናደው ሲሞቱ ምክር ቤቱ ተተኪ እንደራሴ ለመሾም በተሰበሰበ ጊዜ ልጅ ኢያሱ በሂደቱ ውስጥ ሚና እንዲኖረው ጠየቀ። በራስ ተሰማ ናደው ቦታ ማን እንዲሾም እንደሚፈልግ ሲጠየቅ "እኔን ሹሙኝ" ሲል እንደመለሰ ይነገራል። በዚህም የኢያሱ ማኅተም የአያቱን የምኒልክን ማኅተም ተካ እንጂ የንጉሠ ነገሥትነት ማዕረግ አልተጨመረበትም። ኢያሱ በመጀመሪያው ዓመት አገዛዙ ከባድ ተግዳሮቶች ገጥመውታል። ከእነዚህም መካከል የመጀመርያው ራስ አባተ የቤተ መንግሥቱን የጦር መሣሪያ ግምጃ ቤትና ዘመናዊ መሣሪያዎችን በመቆጣጠር መፈንቅለ መንግሥት ለመፈጸም መሞከሩ ሲሆን፤ ነገር ግን የደቡብ አውራጃዎች ወደ ግዛታቸው እንዲመለሱ በመፈቀዱ በይፋ እጁን እንዲሰጥ ተደረገ። ከዚህም በኋላ በክረምት ኢያሱን ለመመረዝ ሙከራ ተደረገ፤ ሙከራው ግን ስኬታማ አልነበረም። በኋላም የልጅ ኢያሱ አባት ንጉሥ ሚካኤል ልጅ ኢያሱን ለመጣል ስለሚደረግ ስለ ሌላ ሴራ መረጃ ደረሳቸውና ፰ ሺህ ወታደሮችን አስከትለው ከደሴ ተነስተው አዲስ አበባ ደረሱ። ይህም ንጉሥ ሚካኤል ልጃቸውን በንጉሠ ነገሥቱ ዙፋን ላይ ለማቆየት ካደረጓቸው ብዙ ሙከራዎች የመጀመሪያው ነበር። በዚህ ጊዜ ልጅ ኢያሱ በአፋር ላይ ይደረጋል የተባለ ወታደራዊ ዘመቻ ለማድረግ በሚል ሽፋን ዋና ከተማዋን ለመልቀቅ ወሰነ፤ ነገር ግን በምሥራቅ ሸዋ እና ወሎ ላይ በመጓዝ ሕዝቡን አገኘ እንጂ ወደ ዘመቻ አልሄደም። በ1904ም ወደ አዲስ አበባ እንደሚመለስ ቃል ገብቶ ነበር፤ ነገር ግን በምትኩ ደብረ ሊባኖስን፣ ከዚያም አዲስ ዓለምን ጎበኘ፣ ከዚያም ደጃዝማች ከበደ ወደ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ያደረጉትን ዘመቻ ተቀላቀለ። ማርከስ ይህንን ከዋና ከተማው ውጭ ያለማቋረጥ መጓዝ መንግሥት ያለ እርሱ መሥራት እንደማይችል ለማረጋገጥ እና ሚኒስትሮቹ ወዲያውኑ አክሊሉን እንዲያቀዳጁት ለማስገደድ ባለው ፍላጎት እንደሆነ ያስረዳል። ልጅ ኢያሱ ወደ ዋና ከተማው ከተመለሰ በኋላ ከጥበቃ ኃላፊ ጋር ተጋጨ፤ ይህም ግጭት በመጨረሻ በአቡነ ማቴዎስ ሽምግልና ተፈታ። የግጭቱም ምክንያት የነበረው ልጅ ኢያሱ አፄ ምኒልክ ገና በሕይወት ሳሉ ወደ ቤተ መንግሥት ካልገባሁ ማለቱ ነበር። ልጅ ኢያሱም ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከተማዋን ለቅቆ በመሄድ አፋር ላይ ዘመቻ ከፈተ። በአባቱም ጉትጎታ ዳግም ወደ አዲስ አበባ ተመለሰ። ዳግማዊ አፄ ምኒልክም ታኅሣሥ 3 ቀን 1906 ዓ.ም. ሞቱ። ለልጅ ኢያሱም የአያቱ መሞት ተነገረው። የንጉሠ ነገሥቱ አስከሬን በንጉሠ ነገሥቱ ቤተ መንግሥት ግቢ ውስጥ ከሚገኘው ሥዕል ቤት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን አጠገብ ባለች ትንሽ ክፍል ውስጥ ገባ። የንጉሠ ነገሥቱም መሞት በቤተ መንግሥት ብቻ የሚታወቅ እንጂ ለህዝብ በይፋ የተነገረ አልነበረም። እቴጌ ጣይቱም ወዲያውኑ ከንጉሠ ነገሥቱ ቤተ መንግሥት ወጥተው በእንጦጦ ተራራ ላይ ወደሚገኘው የቀድሞው ቤተ መንግሥት እንዲሄዱ ተደረገ። የልጅ ኢያሱ አክስት ወይዘሮ ዘውዲቱ ምኒልክም በተመሳሳይ ሁኔታ ከቤተ መንግሥቱ እንዲወጡ ተደረገ። ልጅ ኢያሱ ወደ ቤተ መንግሥት ከገባ በኋላ የዕለት ተዕለት የአገር አመራር ጉዳይ ላይ አያተኩርም ነበርና አብዛኛው የአመራር ሥራ የሚሰራው በሹማምንቱ ነበር፤ በወቅቱም ሀገር ከመምራት ይልቅ ሴት በማብዛትና በራሱ ድሎት ላይ በማተኮር ይታማ ነበር። ይሁን እንጂ የሚኒስትሮች ካቢኔ ከአያቱ ዘመን ጀምሮ ሳይለወጥ የቆየ ሲሆን እስከዚያ ጊዜ ድረስ ሚኒስትሮቹ ከፍተኛ ሥልጣንና ተጽዕኖ ነበራቸው። ልጅ ኢያሱም እነርሱን ያናንቃቸውና ያቃልላቸው ነበር። ብሎም እነሱን እያባረረና የራሱ ምርጫ የሆኑ አዲስ ባለሥልጣናትን በመሾም አዲስ መኳንንትን የመፍጠር ዓላማውን በተደጋጋሚ ይናገር ነበር። የእርሱ መሠረታዊ የዘመናዊነት እርምጃ ዝንባሌ ከአያቱ የድሮ ሚኒስትሮች ወግ አጥባቂነት ጋር ይጋጭ ነበር። በዚህም በዳግማዊ ምኒልክ ጊዜ ይከበሩ የነበሩ የሸዋ ሹማምንት በልጅ ኢያሱ ጊዜ አለመከበራቸው ደስ አላሰኛቸውም። የኢያሱ ያልተጠበቁ ድርጊቶች መኳንንቱን ይበልጥ እንዲርቁ ከማድረግ በቀር ምንም ጥቅም አላስገኙም። ከእነዚህም አንዱ ንጉሣዊ ዘር ያላትን የአጎቱን ልጅ ሹፌሩ ለነበረው ሰው ማጨቱ ነበር። ሌላው ደግሞ ነጋዴ የነበረው ሶሪያዊ ወዳጁን ሐሲብ ይድሊቢን በድሬዳዋ የባቡር ጣቢያ የነጋድራስ (ወይም የጉምሩክ ኃላፊ) ቦታ ላይ መሾሙ ሲሆን ይህም እዚያ የሚሰበሰበውን ከፍተኛ ቀረጥና ጉምሩክ እንዲቆጣጠር አስችሎታል። ይህ ሁሉ ልጅ ኢያሱ በተደጋጋሚ ከዋና ከተማው ከአዲስ አበባ እየጠፋ አገር ለአገር ከመዘዋወሩ ጋር ተዳምሮ በጦር ሚኒስትሩ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ የሚመሩት ሚኒስትሮች እርሱን ለመጣል ምቹ ሁኔታ ፈጠረላቸው። ማጣቀሻ(Reference) https://en.wikipedia.org/wiki/Lij_Iyasu