У нас вы можете посмотреть бесплатно እግዚአብሔር እንግሊዝን የሚበቀልበት ጊዜ ደርሶ ይኾን?በሊቀ ምሑር (ዶክተር) መስከረም ለቺሳ ደበሌ Dr. Meskerem Lechissa Debele или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
እግዚአብሔር እንግሊዝን የሚበቀልበት ጊዜ ደርሶ ይኾን? እንግሊዞች፡ ስለ Prester John አገር ኢትዮጵያ (Utopia/Eutopia) ከሰሙበት ከ12ኛውና 13ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ፡ የፖርቱጋልና የጣልያንን እግር እየተከተሉ ወደኢትዮጵያ እየመጡ፡ ጥያቄ እየጠየቁ፡ አገራቸው እየተመለሱ፡ የሰሙትን መተግበር ሲለማመዱ ቆይተው፡ የመጨረሻውን የኢትዮጵያዊነትን እንጥፍጣፊ ጠራርገው ሊወስዱ በአጼ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት ነበር፡ በተለመደው አክብሮት ለመጨረሻ ጊዜ ብቅ ያሉት። በኹለተኛው ሥእል እንደምታዩት፡ ባሁን ሰዓት በዓለም ላይ ለማንም ሸብረክ የማትለው የእንግሊዟ ንግሥት ኤልሳቤጥ፡ ከባሏ ከልዑል ፊሊፕ ጋር፡ በአጼ ኃይለ ሥላሴና በባለቤታቸው በእቴጌ መነን ፊት በአክብሮት እጅ ስትነሣ ትታያለች። በ1958 መኾኑ ነው። ታድያ፡ ስትመጣ፡ ኢትዮጵያ ላይ ሊመጣ ስላለው ሰይጣናዊ ዐብዮት በሚገባ ዐውቃና የቤት ሥራዋን ሠርታ እያመቻቸቻት ነበር። ንጉሡን "በአገራቸው ላይ ለተከሰተው ረሃብ መፍትሔ አልፈለጉም" ብሎ ኋላ በአደባባይ ያዋረደላት የአገሯ ጋዜጠኛ ጆናታን ዲምቢልቢ ነው። በረሃቡ፣ በደርግ ዐብዮትና በኢሕአዴግ የሥልጣን ሽግግር ወቅት የነበሩት ቁልፍ ሂደቶች ውስጥ የእንግሊዝና የአክስቷ ልጅ የአሜሪካ እጅ አለበት። ይኽን፡ ሽማግሌ ፈረንጆች በግልጽ ይናገራሉ፤ የሚሰማ ከተገኘ። "If you care, we can tell you everything" ይሉናል። ችግሩ ግን፡ we don't care... እና.... we don't ask .... እና.... they know that.