У нас вы можете посмотреть бесплатно በላይ ዘለቀ ሲተዘት Belay Zeleke или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
ጀግናው በላይ ዘለቀ ከአባታቸው ከባሻ ዘለቀ ላቀው እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ጣይቱ አስኔ በ1904 ዓ.ም ተወለዱ። ስለ ትውልድ ቦታቸው ብዙ አወዛጋቢ የሆኑ የተለያዩ መረጃዎች ቢኖሩም ፣ በተወለዱ በአራት ዓመታቸው አባታቸው ባሻ ዘለቀ ላቀው የልጅ እያሱ ባለሟል ሆነው የአንድ ክፍለ ጦር ኃላፊ ስለነበሩ ልጅ እያሱ በተያዙ ጊዜ ከዚያ አምልጠው በቦረና ሳይንት አውራጃ በጨቃታ ወረዳ ልዩ ስሙ ጣቀት መድሉ ከተባለው ቀበሌ ተቀምጠው እንዳሉ ከአንድ ሰው ጋር ግጭት ውስጥ ገብተው በፀብ መካከል የሰው ህይወት ያልፍባቸዋል። ለዚህም ምክንያት ወሎን ለቀው ወደ ጐጃም መጡ። ጐጃምም በተለይ በቢቸና አውራጃ በእነማይ ወረዳ ልዩ ስሙ ለምጨን ከተባለው ቀበሌ ተቀመጡ። ብቸና ውስጥም ተቀምጠው ሳለ እርሳቸውን የሚያስስ ልዩ ጦር በጥቆማ ወደ አካባቢው ተላከ። ከዚህ ጦር ጋርም ከፍተኛ ውጊያ ተደረገ። በዚህ ውጊያ ወቅት በላይ ዘለቀ እና እጅጉ ዘለቀ ልጆች ቢሆኑም ተኩሱን እያዩ የሚወድቁትን ጥይቶች ይቆጥሩ ነበር። ከውጊያው በኋላም የበላይ ዘለቀ አባት ተመተው ይወድቃሉ። ይሞታሉ። እነ በላይ ዘለቀም ካለ አባት ከእናታቸው ከወ/ሮ ጣይቱ አሰኔ ጋር ማደግ ይጀምራሉ። ከፍ ሲሉም የአባታቸውን ገዳይ እና አስጠቁሞ እየመራ ያስገደላቸው ማን እንደሆነም ለማወቅ ማሰስ ጀመሩ። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሳሉ ፋሺስት ኢጣሊያ በ1928 ዓ.ም ኢትዮጵያን ወረረች። በላይ ዘለቀ በወቅቱ የ24 ዓመት ወጣት ነበሩ። ሀገርን የወረረውን የኢጣሊያን ጦር ለመውጋት ቆርጠው ተነሱ። በወቅቱ ከ200 እስከ 300 ያህል ጦር በስራቸው ሊያሰባስቡ ቻሉ። በወቅቱም የአካባቢውን ሕዝብ ሰብስበው የሚከተለውን ንግግር አደረጉ። “እኔ የዘለቀ ልጅ የምታዩትን የአባቴን አንድ ጥይት ጐራሽ ናስማስር ጠብመንጃዬን ይዤ በሀገር በረሃ የአላዩን ወንዝ ይዤ፣ የአለቱን ድንጋይ ተንተርሼ፣ አሸዋውን ለብሼ ዋሻውንና ተራራውን ምሽግ አድርጌ የመጣውን ጠላት እቋቋመዋለሁ፤ እንጂ እንኳንስ እናንተ የእናቴ ልጆች እጅጉ እና አያሌው ጥለውኝ ሄደው አንድ እኔ ብቻ ብቀርም ከዓላማዬ ፍንክች አልልም። እናት ሐገሬ ኢትዮጵያ ስትደፈር ከማየት ሞቴን እመርጣለሁ። የፈራህ ልቀቀኝ! ለውድ እናት ሀገርህ መስዋዕት ለመሆን የምትፈልግ ሁሉ እኔን ተከተለኝ”.....