У нас вы можете посмотреть бесплатно ዓላማ መር ህይወት- ቀን 16_Purpose driven Life - Day 16_ alama mer hiywot- ken 16 или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
16 ቀን ዋናው ነገር “ያለኝን ሁሉ ለድሆች ብሰጥ ስጋዬን ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ፡፡” 1ቆሮ 13:3 የሕይወት ዋና ነገር ፍቅር ነዉ፡፡ እግዚአብሔር ፍቅር ስለሆነ በምድር ላይ ስንኖር ማፍቀር እንድንማር ነዉ ሚፈልገዉ፡፡ይበልጥ እርሱን ምንመስለዉም ስናፈቅረዉ ነዉ፡፡በመሆኑም ሸቅር ፣እሱ የሰጠን የትእዛዝ ሁሉ መሠረት ነዉ፡፡ እግዚአብሔርን በፍፁም ልባችን በፍፁም ነፍሳችን እና ባልንጀራችንን እንደራሳችን እንድንወድ ታዘናል፡፡ ገላ 5:14 ወንድሞችን ውደዱ 2ጴጥ 2:17 ለአማኞችና በዉጭ ላሉ ግን ለአማኞች ፍቅር እንዲኖረን ይነግረናል ጴጥሮስ በመልክቱ ፡፡ ለምንድነዉ በቅድሚያ እነሱ ሊወደዱ የሚገባቸዉ ?ምክያቱም ቤተሰብ ከሌላ ነገር ይልቅ ፣እርስ በእርስ በመዋደድ አማካይነት እንዲታወቅ እግዚአብሔር ይፈልጋል ፡፡ለአለም የሚታየዉ ትልቁ ምስክርነት የእምነት አቋማችን ሳይሆን እርስ በእርስ ያለን ፍቅር መሆኑን እየሱስ እርስ በእርሳችሁ ብትዋደዱ ደቀ መዛሙርቴ እንደ ሆናችሁ ሰዎች ሁሉ ያዉቃሉ ብሎናል ዮሐ 13:35 በሕይወታችን ልናከናዉን የምንችለው ከሁሉ የሚበልጥ ተግባር ፍቅር ነዉ፡፡ ፍቅርን ተከታተሉ 1ቆሮ 14:1 ህይወት ያለ ፍቅር ፋይዳ ቢስ ነዉ፡፡ ፍቅር ለዘላለም ይኖራል ፍቅር ቅርስ ነዉ፡፡በምድር ላይ የምትተወዉ ቀጣይ ተፅዕኖ ፣ሀብትህ ወይም ስኬት ሳይሆን ለሌሎች የምታደርገው ነገር ነዉ፡፡ ዋናው ነገር ደግሞ የምታደርገው ነገር ሳይሆን በድርጊቱ ዉስጥ የምትጨምረዉ ፍቅር ነዉ፡፡ የፍቅር የላቀ መገለጫ ጊዜ ነዉ፡፡ የነገሮች ጠቃሚነት የሚለካው ፣ለነገሮች በምንመድበዉ የጊዜ ነዉ፡፡ለአንድ ነገር ጊዜህን ቁጥር ያ ነገር ለአንተ ያለዉን ፋይዳና ጠቃሚነት ይበልጥ ትገልጣለህ፡፡ ጊዜ ተወስኖ የተሰጠህ በመሆኑ ፣ከሁሉ የበለጠ ክቡር ስጦታ ነዉ፡፡ ለአንድ ሰዉ የምትሰጠዉ ትልቁ ነገር ጊዜህ ነዉ፡፡ እንደገና የማታገኘዉን የሕይወትህ አንድ ክፍል መስጠትህ ነዉ፡፡ጊዜህ ሕይወት ነዉ፡፡ የፍቅር ፍሬ ነገር ፣ለሌሎች የምናስበዉ ፣የምናደርገዉ ወይም የምንለግሳቸዉ ነገር ሳይሆን ከእኛነታችን የምንሰጠው መጠን ነዉ፡፡ ተወዳጁ የፍቅር ስጦታ እንቁ ፣አበባ ወይም ቸኮሌት አይደለም፡፡ ከልብ የሆነ ትኩረት ነዉ፡፡ ፍቅር እራስህን እስክትረሳ ድረስ በተፈቃሪዉ ላይ እንድታተኩር ያደርግሃል፡፡ ከሁሉ የተሻለ ማፍቀሪያ ጊዜ አሁን ነዉ፡፡ ይህ እድል ለምን ያህል ጊዜ ካንተ ጋር እንደሚቆይ አታዉቅም ሁኔታዎች ይለዋወጣሉ ሰዎች ይሞታሉ ህፃናት ያድጋሉ፡፡ቀኖቹ ክፉዎች ናቸዉ፡፡ በሪክ ዋረን አላማ መር ህይወት