У нас вы можете посмотреть бесплатно ፕሮፌሰር ሰለሞን ተፈራ - ክፍል 2 - የአእምሮ ሃኪም ፣ የሱስና ተዛማጅ ህመሞች ስፔሺያሊስት | S1 EP18 или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
የዚህ ሳምንት እንግዳችን በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሱስ እና ተዛማጅ ችግሮች ስፔሻሊስት ሀኪም እና ተመራማሪ እንዲሁም ሬናሰንት የአዕምሮ ህክምናና ተሃድሶ ማዕከል መስራች እና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ሰለሞን ተፈራ ጋር ያደረግነዉ ቆይታ እነሆ፡፡ የህክምና ትምህርታቸዉን በጅማ ዩኒቨርሲቲ የተማሩት ፕሮፌሰር ሰለሞን፣ የሳይካትሪ ስፔሻሊቲ ስልጠናቸዉን በቶሮንቶ-አዲስ አበባ ጣምራ ፕሮግራም፦ ከሱስ ሳይኪያትሪ የክሊኒካል ፌደሬሽን አግኝተዋል። ከዚያም በስዊድን በሚገኘው በኡሜዮ ዩኒቨርሲቲ በሳይካትሪ ኤፒዲሚዮሎጂ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በማጠናቀቅ በዚህ ስፔሻሊቲ የሰለጠኑ የመጀመሪያውና ብቸኛው ኢትዮጵያዊ ሐኪም ናቸዉ። ዓለም አቀፋዊ እውቀትን ከኢትዮጵያ የአእምሮ ጤና ገጽታ ጋር በማዋሀድ ታላቅ አስተወፆን እያበረከቱ ይገኛሉ። በዕፅ እና ሌሎች ሱሶች ላለባቸው ግለሰቦች ሁለንተናዊ እንክብካቤ የሚሰጠዉን የሬናሰንት የአዕምሮ ህክምናና ተሃድሶ ማዕከል መስራች እና ክሊኒካል ዳይሬክተር ናቸው። በሱስ እና ተዛማጅ ችግሮች ለተጎዱ ግለሰቦች እርዳታን በመስጠት እንዲሁም የአእምሮ ጤና እንክብካቤን ለማዳበር በመስራት ግንባር ቀደም ናቸዉ። ከዚህም በተጨማሪ በአዲስ-አበባ ዩኒቨርስቲ የአዕምሮ ህክምና ፕሮፌሰር በመሆን የአዕምሮ ጤና ባለሙያዎች ለመቅረጽ ይሰራሉ። በሀገር ደረጃ ያሉ ፖሊሲዎችን በመቅረፅ ረገድ ሱስን ፣ አደንዛዥ ዕፆች እና ተያያዥ ስነ-ልቦናዊ እና ማህበራዊ ችግሮችን ለመቅረፍ እና የለዉጥን ተግባራዊነት በማስፈፀም ረገድ በርካታ አስተዋጾ እያደረጉ ይገኛሉ። በክፍል አንድ የፕሮፌሰር ሰለሞን የኃላ ታሪክ እና ልምድ፣ አስተዳደጋቸውን ፣ ተጽዕኖ ያሳደረባቸውን ክስተቶች፣ እና ሙያዊ ግንዛቤያቸውን የሚቃኘውን አጓጊ ውይይት ይከታተሉ። Our guest this week is Ethiopia’s first medical doctor and researcher specializing in addiction and related disorders. He is also the founder and director of the Renaissance Center for Mental Health and Recovery - Professor Solomon Teferra. Professor Solomon earned his medical degree from Jimma University and completed his psychiatry specialty training through the Toronto–Addis Ababa Collaborative Program, where he received a Clinical Fellowship in Addiction Psychiatry. He later obtained his PhD in Psychiatric Epidemiology from Umeå University in Sweden, making him the first and only Ethiopian physician formally trained at this level in addiction treatment and specialty. His groundbreaking work integrates global knowledge with the Ethiopian mental health landscape. As the founder and clinical director of the Renascent Mental Health and Rehabilitation Center, he offers dual-care services for individuals struggling with substance use and other related challenges. He has been at the forefront of improving access to addiction support and expanding the scope of mental health care in Ethiopia. In addition to his clinical work, Professor Solomon is a professor of psychiatry at Addis Ababa University, where he trains the next generation of mental health professionals. He also contributes to shaping national mental health policies, with a focus on substance use, behavioral disorders, and their psychological and social impacts. His work has played a key role in advancing practical reforms and policy change. In Part two, we explore different addictions and their repercussions, the pioneering leadership roles he has taken on, and the impact of his work in the field of addiction and mental health in Ethiopia. … Renascent Mental Health and Rehabilitation Center/ሬናሰንት የአዕምሮ ህክምናና ተሃድሶ ማዕከል http://renascentrehabcenter.com/ Tel: +251 941 77 60 60 +251 978 49 60 60 +251 965 47 02 02 Email: [email protected] Location: Legetafo, Addis Ababa, Ethiopia … ምዕራፎች 0:00 መግቢያ 1:00 ብዙ አይነት እጾች 9:40 የሕክምና ወይም ሕጋዊ እጾች (ካናቢስ/ማሪዋና) 15:43 ስለ ሽሻ 18:46 ስለ አልኮል መጠጥ 25:10 ስለ ጫት 27:05 ሲጋራ ፣ ቬፕ እና ትንባሆ 33:00 ማህበራዊ ሚዲያ እና ከኢንተርኔት ጋር የተያያዙ ሱሶች 38:40 ለሱስ ህክምና የት እንሂድ? 45:40 AA (alcholics anonymous) 51:20 የህዝብ ጤና (Public Health) 58:00 በትምህርት ቤት ውስጥ የአደንዛዥ ዕፅ 1:00:20 ቀጣይ ባለሙያዎችን ማስተማር- ሱስ የአእምሮ ሐኪም የወደፊት 1:07:00 ማህበረሰብና የእምነት ተቋማት፣ የሚድያዎች ሚና 1:12:54 የመጨረሻ አስተያየቶች … #addictionrecovery #psychiatrist #mindsetpodcast #ethiopia #podcast #drmehretdebebe … ማይንድሴት ፖድካስት:- በዶክተር ምህረተ ደበበ አቅራቢነት ፣ ጠቃሚና አስተማሪ በሆኑ ርዕሰ ጉዳዮችን ከአንጋፋ ባለሙያዎች ፣ የሃሳብ መሪዎች እና የየተለየ ኢንዱስትሪ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጋር ጥልቅ ውይይቶችን ያቀርብልዎታል። Mindset Podcast, hosted by Mehret Debebe, brings you in-depth conversations with renowned experts, thought leaders, and industry professionals touching on important topics.