У нас вы можете посмотреть бесплатно ዓላማ መር ህይወት- ቀን 13_Purpose driven Life - Day 13_ alama mer hiywet- ken 13 или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
13ተኛ ቀን እግዚአብሔርን የሚያስደስት አምልኮ "ጌታ አምላክህን በፍፁም ልብህ ፣በፍፁም ነፍስህ ፣በፍፁም ሐሳብህና በፍፁም ኃይልህ ዉደድ፡፡" ማር 12:30 እግዚአብሔር ሁሉንተናህን ይፈልጋል፡፡ የአንተን አንድ ክፍል ብቻ አይደለም የሚፈልገው ፡፡ልብህን በሙሉ ፣ነፍስህን በሙሉ ፣ አእምሮህን በሙሉ ፣እና ኃይልህን በሙሉ ይፈልጋል ፡፡ 👌እግዚአብሔር ግማሽ ልብ የሆነ መሰጠትህን ፣ከፊል ታዛዥነትህን ፣እና ትርፍ ጊዜህን እንዲሁም ገንዘብህን አይደለም የሚፈልገው፡፡ አምልኮ ስለ እግዚአብሔር በሚኖረን አስተሳሰብ ላይ ሳይሆን ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ እዉነት ላይ መመስረት አለበት ፡፡እየሱስ ለሳምራዊቷ ሴት "በእዉነት የሚሰግዱ ለአብ በመንፈስና በእዉነት የሚሰግዱበት ጊዜ ይመጣል ፤አሁንም መቶአል ፣አብም እንደዚህ በእውነት የሚሰግዱለትን ይፈልጋል" ዮሐ 4:23 በእዉነት ስናመልከዉ እግዚአብሔር ደስ ይለዋል፡፡ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል 1ሳሙ 16:7 👍አምልኳችን በተግባር ሲሆን እግዚአብሔር ደስ ይለዋል ፡፡ ሰዉነታችሁን ቅዱስና እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ህያዉ መስዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርህራሄ አለምናችኃለዉ፡ እርሱም ለአይምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነዉ፡፡ሮሜ 12:1 ጌታ እሁድ እሁድ "ክርስቲያን ወታደር ሆይ !ወደ ፊት ተጓዝ"ሰኞ ሰኞ ኮብላይ ወታደር እንድንሆን አይፈልግም እራሳችንን ቅዱስ መስዋዕት እንድናደርግ ለአለም እንድንሞት ይፈልጋል ፡፡ ✅ እዉነተኛ አምልኮ መሰረቱ የእግዚአብሔር ቃል ነዉ፡፡ አምልኮ ዋጋ ያስከፍላል አምልኮ ከሚያስከፍለዉ ዋጋ አንዱ እራስ ወዳድነታችን ነዉ፡፡እራስህንና እግዚአብሔርን በአንድ ጊዜ ከፍ ከፍ ማድረግ አትችልም፡፡በሌሎች ለመታየት ወይም እራስህን ለማስደሰት ስትል ልታመልከዉ አትችልም ፡፡በመሆኑም የአምልኮ ትኩረትህን ከራስህ ላይ ማንሳት አለብህ፡፡ የማመስገን ፍላጎት ባይኖርህ እንኳን እግዚአብሔርን ስታሞግስ ፣ደክመህ ሳለ ልታመልከዉ ከመኝታህ ስትነሳ ፣ወይም ድክም ብሎህ ሳለ ሌሎችን ስትረዳ ፣ለእግዚአብሔር የአምልኮ መስዋት በማቅረብ ላይ ነህ፡፡ በዚህ ትምህርት መጋቢዉ "የአምልኮ ልብ" የሚል ርዕስ ያለዉ መዝሙር ፃፈ ከዝማሬ የሚበልጥ መጣሁ ይዤልህ ዝማሬን ብቻ ሳይሆን ከኔ የጠየቅህ ከሚታዩ ነገሮች ይልቅ ጠልቀህ ልቤን በመመርመር ላይ ነህ የቁም ነገሩ ልብ ፣የልብ ቁም ነገር ነዉ፡፡ 🔔እግዚአብሔር አሁን ይበልጥ የሚያስደስተዉ የቱ ነዉ ?ከሕዝብ ጋር የማደርገው ወይስ የግል አምልኮዬ??ስለዚህ ነገር ምን ላድርግ?? በሪክ ዋረን አላማ መር ህይወት