У нас вы можете посмотреть бесплатно ግራዋ ቅጠል ጥቅም 🍂የግራዋ ጥቅሞች 🌹የግራዋ ጥቅም 🌻የግራዋ ቅጠል ጥቅም или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
ግራዋ ኢትዮጵያና አፍሪካ ውስጥ በብዛት የሚገኝ ተክል ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ ሰዎች ባህላዊ መጠጦች እንደ ጠላና ጠጅ ያሉትን ከማዘጋጀታቸው በፊት እቃዎቹን በግራዋ ቅጠል ያጥባሉ። #ግራዋ ቅጠል ጥቅም#የግራዋ ጥቅሞች#የግራዋ ጥቅም#የግራዋ ቅጠል ጥቅም ግራዋ ከእቃ ማጠቢያነት ባለፈ ለቆዳና ለፀጉር ብዙ ጥቅሞች አሉት በዚህ ቪድዮ የተወሰኑትን የግራዋ ጥቅሞች እናያለን ግራዋ ቅጠል በቫይታሚን ኤ ሲ ኢ ቢ1 እና ቢ2፣ ካልሲየም፤ ዚንክ፤ አይረን፤ ፎስፎረስ፣ኮፐር፤ ፕሮቲንና ሚነራሎች የበለፀገ ነው እንዲሁም ፀረባክቴርያ፤ ፀረኦክሲዳንትና ፀረፈንገስ ፀረጥገኛ ህዋስ ባህሪ አለው በዚህ የተነሳ ግራዋ ለተለያዩ የቆዳ ችግሮች መፍትሄ ይሰጣል ለምሳሌ ለቆዳ ኢንፌክሽኖች ለሽፍታ፣ ጭርት፣ችፌ የመሳሰሉትን ያጠፋል. ጥቅሞቹን በዝርዝር ስናይ ደግሞ ለብጉር: ግራዋ ቅጠል ውስጥ ያሉት ቫይታሚኖች መርዛማ ንጥረነገሮች ከሰውነት እንዲወገዱ ያግዛሉ በዚህ ምክንያት ብጉር ከቆዳ ላይ እንዲጠፋና ቆዳ እንዲለሰልስ ያደርጋል ለጋ የግራዋ ቅጠሎችን ፈጭቶ እንደማስክ አዘጋጅቶ ፊትን መቀባት ጥሩ ውጤት ያስገኛል Pro tip: የግራዋን ቅጠሎች አጥቦ ማድረቅና ፈጭቶ ዱቄቱን በጠርሙስ አስቀምጦ እስከ 1 ወር ድረስ ለማስክ መጠቀም ይቻላል 1 ማንኪያ የግራዋ ዱቄት ከትንሽ ሙቅ ውሃ ጋር አድርጎ ማቡካትና ፊትን ቀብቶ 15 ደቂቃ አቆይቶ መታጠብ ይቻላል የግራዋ ማስክ ብጉርን ለማጥፋት ከመርዳትም አልፎ ቆዳን ከጎጂ ኬሚካሎች በመጠበቅ ቆዳ ቶሎ እንዳያረጅ ይረዳል ለብጉርና ለነጠብጣቦች ግራዋ በተፈጥሮአዊ መንገድ በአጭር ጊዜ ቆዳው ሳይጎዳ ጥርት ያለ ቆዳ እንዲኖረን ያስችላል ቆዳም ቶሎ እንዳያረጅ ይከላከልለታል ከ10-15 የሚሆን የግራዋ ቅጠል ፤ 4 የሾርባ ማንኪያ ውሃ፤ ትንሽ ንፁህ እርድ (ምንም ቅመም ያልተጨመረበት) 2 ማንኪያ የእሬት ፈሳሽ aloe Vera gel ሁሉንም አንድ ላይ አድርጎ ፈጭቶ በንፁህ ፊት ላይ መቀባትና ትንሽ ማሸት በኻላም 20 ደቂቃ አቆይቶ መታጠብ ይሄን ማስክ በሳምንት 3 ጊዜ በመቀባት ብጉርንና ጥቋቁር ነጠብጣቦችን ማጥፋት ይቻላል ለሚያበራ ቆዳ የግራዋ ቅጠል ከ10-15 ፤ የእሬት ፈሳሽ 2 የሾርባ ማንኪያ፤ 1ማንኪያ የሎሚ ጭማቂ፤ 1 ማንኪያ ማር የግራዋውን ቅጠሎች ከትንሽ ውሃ ጋር መፍጨትና የእሬቱን ፈሳሽ፤የሎሚውን ጭማቂና ማሩን መጨመርና መፍጨት ከዛም በንፁህ ፊት ላይ ውህዱን ቀብቶ ከ2-4 ለሚሆን ደቂቃ በክቡ ማሸት ከዛ ለ20 ደቂቃ አቆይቶ መታጠብ ግራዋ ቅጠል ብዙ ቫይታሚኖችና ማእድናትን ስለያዘ ብጉርና፤ ነጠብጣቦች እንዲጠፉ በማድረግ ቆዳ የሚያበራና ለስላሳ እንዲሆን ያደርጋል ይሄን ማስክ በሳምንት 3 ጊዜ ማድረግ ይቻላል የፊት ማስክ: እርጥቡን የግራዋ ቅጠል ትንሽ ውሃ ጨምሮ እስኪልም መፍጨትና ፊትን አዳርሶ መቀባት ፈሳሹ የቆዳ ቀዳዳዎችን ዘልቆ እንዲገባ ለ20 ደቂቃዎች ማቆየትበንጹህ ውሃ መታጠብ ይህንን ማስክ በየቀኑ በመቀባት በጣም በአጭር ጊዜ ውስጥ ለውጥ ማየት ይቻላል ጥርት ላለ ፊት ከሻወር በፊት የግራዋን ቅጠል አጥቦ በእጅ በማሸት አረፋ እንዲወጣው ማድረግና ይሄን አረፋ ቆዳ ላይ ተቀብቶ ለ30 ደቂቃ አቆይቶ መታጠብ ለሰውነት ቆዳ ጠቃሚ ነው ይህን በየቀኑ በማድረግ የሰፉ የቆዳ ቀዳዳዎች ብጉር ጥቁር ነጠብጣቦች ጭርትና የመሳሰሉት ታሪክ ሆነው ይቀራሉ በግራዋ ቅጠል መታጠብ ቆዳ እንዲያበራ ከማድረግ ባለፈ ፈገግ ያለ ቀለም እንዲይዝ ይረዳል ቆዳን የማንጣት ባህሪ አለው ግራዋውን ጨምቆ ለፊት መታጠቢያነትም መጠቀም ይቻላል የግራዋን ጭማቂ በጥጥ እየነከሩ ፊትን መቀባትና ለ30 ደቂቃዎች አቆይቶ መታጠብ ቆዳን ጥርት ያደርጋል የግራዋን ጭማቂ ስታስቀምጡ ፍሪጅ ውስጥ ከ5 ቀን በላይ ማስቀመጥ አይኖርባችሁም ለፀጉር ግራዋ ፀጉር እንዳይበጣጠስ እንዲያንፀባርቅ፡ ቀለሙን ጠብቆ እንዲቆይ በተለይ ጥቁረቱን፡ ጠብቆ እንዲቆይ፣ እንዳይደርቅና እንዳይሰባበር ይረዳል እርጥቡን የግራዋ ቅጠል ፈጭቶ ውሃውን ለፀጉር መታጠቢያነት በመጠቀም የፀጉርን እድገት ማፋጠን ይቻላል የግራዋን ቅጠል በእጅ በደንብ ማሸት ውሃው እስኪወጣና አረፋማ እስኪሆን ጨምቆ በእቃ ማጠራቀምና በዚህ ፈሳሽ ፀጉርን መታጠብ ከዛም በንጹህ ውሃ ማለቅለቅ ይህን ደጋግሞ በማድረግ ፀጉር ቶሎ እንዲያድግ መርዳት ይቻላል ግራዋን እንደ ሻምፖ… ንፁህ የግራዋ ቅጠል ቀጥፎ ማጠብና ፈጭቶ በማጥለያ አጥልሎ ጠርሙስ ውስጥ መክተት ከፈለጋችሁ ኮኮናት ወይም የወይራ ዘይት አብራችሁ ጨምራችሁ ፀጉርን በተለይ ደግሞ የራስ ቅል ቆዳን ቀብቶ ለ1 ሰአት ያክል ሸፍኖ ማቆየትና በውሃና በሳሙና መታጠብ ነው ይሄ ማስክ ፀጉርን አንፀባራቂና ብዙ እንዲሆን ያደርጋል ፤ እንዳይያያዝ እንዲፍታታ ያረጋል እንደኮንዲሽነር ፤ ፎረፎርን ያጠፋል ፤ ለሚያሳክክና ጭርት ላለበት የራስ ቅልም መፍትሄ ይሰጣል ይሄን ማስክ በሳምንት 2 ጊዜ መጠቀም ይቻላል ግራዋ ለሁሉም አይነት የቆዳ አይነቶች የሚሆን ቢሆንም ሴንሲቲቭ የሆነ የቆዳ አይነት ካላችሁ ግን የቆዳ ሃኪም መጀመሪያ ሳታማክሩ ግራዋ ቅጠልን ለቆዳችሁ አትጠቀሙ / @lavender1626